ሊ ካንግ-ኢን የ2026 የእስያ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ምርጥ ዓለም አቀፍ ተጫዋች ኾኖ ተመረጠ።

0
39

የደቡብ ኮሪያ ብሔራዊ ቡድን እና የአትሌቲኮ ማድሪድ አማካይ ሊ ካንግ-ኢን፣ በባንኮክ በተካሄደው የ2026 የእስያ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (AFC) የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ የዓመቱ ምርጥ ዓለም አቀፍ ተጫዋች (International Player of the Year) በመባል ተመርጧል።

የ25 ዓመቱ ሊ ካንግ-ኢን፣ ሽልማቱን በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ ያሸነፈ የመጀመሪያው ተጫዋችም ኾኗል። እንዲሁም ይህን ሽልማት 4 ጊዜ ካሸነፈው ከሶን ሂዩንግ-ሚን ቀጥሎ ሽልማቱን ከአንድ ጊዜ በላይ ያሳካ ሁለተኛው ተጫዋች መኾንም ችሏል። በመጨረሻው እጩነት የቀረቡትን የፖርቶ ተጫዋች የሀገሩን ልጅ ህዋንግ ኢን-ቢዮም እና የሊል ተጫዋች የጃፓኑን አጥቂ አያሴ ኡኤዳን በማሸነፍ ነው ክብሩን የተቀዳጀው።

ተጫዋቹ ባለፈው የ2025/26 የውድድር ዘመን ከፓሪስ ሴንት ጀርመን (PSG) ጋር የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እና ሊግ 1ን ጨምሮ ዋንጫዎችን ካሳካ በኋላ፣ በክረምቱ ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ተዛውሮ በላሊጋው እና በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረጉ ለድሉ አብቅቶታል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_11_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here