ከወራጅ ቀጣናው ለመትረፍ የሚደረገው ፉክክር አጓጊ ኾኗል?

0
54

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ገና 10 ጨዋታዎች ቢደረጉም፣ በወራጅ ቀጣና ውስጥ የሚገኙት ክሪስታል ፓላስ፣ ሰንደርላንድ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ከወዲሁ ስጋት ውስጥ ገብተዋል።

ክሪስታል ፓላስ ቶማስ ፍራንክን፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ደግሞ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን በአዲስ አሠልጣኝነት ሾመዋል፤ ሰንደርላንድ ግን በአሠልጣኙ ሬጂስ ለ ብሪስ ላይ እምነቱን አሳድሯል።

ሊጉ 20 ቡድኖችን መያዝ ከጀመረበት ከ1995/96 ወዲህ፣ በ10 ጨዋታዎች ግርጌ ላይ ከተቀመጡ ቡድኖች መካከል መትረፍ የቻሉት 44በመቶ ብቻ ናቸው።

ባለፉት ስምንት ተከታታይ የውድድር ዓመታት፣ በ10ኛው ሳምንት ግርጌ ከነበሩት ሦሥት ቡድኖች መካከል ከአንድ በላይ ቡድን ከመውረድ የተረፈበት አጋጣሚ የለም።

ታዲያ የእነዚህ ቡድኖች በታሪክ አጋጣሚ እንደተከሰተው ይኾናል ወይስ የተለየ ክስተት ይፈጠራል የሚለው አጓጊ ኾኗል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_10_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here