በዓለም ወጣቶች ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ያኮሩ አትሌቶች ዛሬ በባሕር ዳር እውቅና ይሰጣቸዋል።

0
65

በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው የወጣቶች ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ አምሥት ወርቅ እና ሦሥት ብር በድምሩ ስምንት ሜዳሊዎችን በማግኘት በአትሌቲክስ ከዓለም ሀገራት ቀዳሚ ኾና ማጠናቀቋ ይታወሳል።

ይህንን ውጤት ያስመዘገቡ አትሌቶች ባሕር ዳር ከተማ የገቡ ሲኾን ዛሬ ኢትዮጵያ ከሞዛምቢክ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚያደርጉትን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ይታደማሉ።

ምሽት ላይ ደግሞ የእራት ግብዣ እና የዕውቅና መርሐ ግብር እንደተዘጋጀላቸው ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_08_2019_ዓ_ም

በኃይሌ አበራ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here