“በመከላከል ሳይኾን በማጥቃት አሸንፈን ሦሥት ነጥብ ለማግኘት ወደ ሜዳ እንገባለን” አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

0
92

ለ2027 አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የኢትየጵያ ብሄራዊ ቡድን 4ኛ ዙር ወሳኝ ጨዋታውን ዛሬ ቀን 10፡00 ያከናውናል፡፡

ይህን ጨዋታ አስመልክቶ የዋሊያዎቹ ዋና አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ከሰጠው ሃሳብ መካከል፦

የጨዋታ ግብ፦ ዋልያዎቹ ዛሬ በባሕር ዳር ስታዲየም ከሞዛምቢክ ጋር ሲጫወቱ በመከላከል ሳይኾን በማጥቃት አሸንፈው ሦሥት ነጥብ ለማግኘት ይገባሉ።

የቡድን ዝግጅትና ጤና፦ የመጨረሻው ልምምድ የተሳካ ሲኾን ከሁለት ተጫዋቾች በስተቀር ሁሉም ሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ።

ተጋጣሚን ማጥናት፦ የሞዛምቢክ ዋነኛ አደጋ ፈጣን የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ መኾኑን አሠልጣኙ ጠቁመዋል።

ራስን መቻል፦ በሌሎች ውጤት ጥገኛ ሳይኾኑ በራሳቸው ጥረት እና አቅም የማለፍ ዕድላቸውን መወሰን እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የደጋፊ ተጽዕኖ፦ ደጋፊው ለቡድኑ ወሳኝ ነው። በመኾኑም በደጋፊው ታጅበን በልምምድ የተሠራውን በሜዳ ላይ በተግባር ማሳየት ወሳኝ ነው።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_08_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here