ለ2027 አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የኢትየጵያ ብሄራዊ ቡድን 4ኛ ዙር ወሳኝ ጨዋታውን ዛሬ ቀን 10፡00 ያከናውናል፡፡
ይህን ጨዋታ አስመልክቶ የዋሊያዎቹ አንበል ጋቶች ፓኖም ከሰጠው ሃሳብ መካከል፦
ጥሩ ስነ-ልቦና እና ዝግጁነት፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከሞዛምቢክ ጋር ለሚያደርጉት ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በጥሩ ሞራልና ዝግጁነት ላይ ይገኛሉ።
ያለፈው ድል እና ቀጣይ ትኩረት፡ ቡድኑ በማፑቶ ያደረገውን ጨዋታ በ3 ነጥብ ድል አጠናቆ፣ አሁን ሙሉ ትኩረቱን በሜዳው በሚያደርገው የዛሬ ጨዋታ ላይ አድርጓል።
የጨዋታው ወሳኝነት፡ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ እና 3 ነጥብ ማግኘት ዋልያዎቹ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማለፍ እድላቸውን በእጅጉ ያሰፋዋል።
ለደጋፊዎች የቀረበ ጥሪ፡ አምበሉ ጋቶች ፓኖም ደጋፊዎች እንደተለመደው “12ኛ ተጫዋች” ኾነው ስታዲየም በመገኘት ቡድኑን እንዲያበረታቱ ጥሪ አቅርቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



