ለሌላ ድል ባሕር ዳር የሚገኙት ዋልያዎቹ፡፡

0
71

ለ2027 አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የኢትየጵያ ብሄራዊ ቡድን ወሳኝ ጨዋታውን ዛሬ ቀን 10፡00 ያከናውናል፡፡

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 4ኛ የምድብ ጨዋታ ዋልያዎቹ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ዛሬ ከሞዛምቢክ አቻቸው ጋር ሲጫወቱ ለ አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ያላቸውን ዕድል ለማስፋት በማሰብ ነው፡፡

በከቀናት በፊት በምድብ 3ኛ ጨዋታቸው ማፑቶ ላይ ሞዛምቢክን በሜዳዋ በከነአን ማርክነህ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በማሸነፍ ወሳኝ ድል ይዘው የተመለሱት ዋልያዎቹ ይሄንን ተመሳሳይ ብሄራዊ ቡድን በሜዳቸው እና በደጋፊያቸው ፊት ይገጥማሉ፡፡

3 ነጥብ ማግኘት ብቸኛ አማራጭ ለዋልያው በኾነው በዚህ ወሳኝ መርሐግብር የዋልያዎቹ አለቃ አሠልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ 3 ነጥብ ለማግኘት እና ሕዝቡን ለማስደሰት ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ከጨዋታው አስቀድሞ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

በሜዳቸው ዋልያዎቹን ሲገጥሙ ያቀዱት እና ሜዳ ላይ የኾነው የተለየባቸው የሞዛምቢኩ አቻቸው አሠልጣኝ ቺኪንሆ ኮንዴ በበኩላቸው ጨዋታውን በብልጠት ድል አድርጎ ለመወጣት እንደሚሞክሩ በቅድመ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ተናግረዋል፡፡

ትናንት ሴኔጋል ሱዳንን 4 ለ 2 በማሸነፍ የምድቡን መሪነት በ10 ነጥብ መያዟ አሁን ላይ የ2ኛነት የምድብ ቆይታን ለማረጋገጥ ፉክክሩ በዛሬ ተጋጣሚዎች ኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ መካከል ኾኗል፡፡

ሞዛምቢክ በ4 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ዋልያዎቹ በ3 ነጥብ 4ኛ ላይ ናቸው፡፡ የዛሬ አሸናፊ ብሄራዊ ቡድንም ከሴኔጋል ቀጠሎ ለመቀመጥ እና 3ኛ ኾኖ ከምድብ ለማለፍ ዕድሉን የሚያሰፋበት ይኾናል፡፡

ይህ ወሳኝ ጨዋታም እንደተለመደው በደጋፊዎቹ ድባብ ታጅቦ ይከናወናል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ታዲያ ኢትዮጵያ የማፑቶ ድሏን ታስቀጥላለች ወይስ ቁጭት ያደረባቸው ሞዛምቢኮች ያሸንፋሉ ለሚለው ጥያቄ 10፡00 ላይ የሚካሄደው ጨዋታ ምላሽ አለው፡፡

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_08_2019_ዓ_ም

በሐናማርያም መስፍን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here