አንጋፋው አጥቂ ሮሜሉ ሉካኩ ራሱን ከቤልጅየም ብሄራዊ ቡድን ማግለሉን አስታወቀ።

0
74

የ33 ዓመቱ አጥቂ ላለፉት 15 ዓመታት በ135 ጨዋታዎች ላይ ለሀገሩ ተሰልፏል።

በእነዚህ ጨዋታዎችም 95 ግቦችን በማስቆጠር የብሄራዊ ቡድኑን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አግቢነት ክብር ተቀዳጅቷል።

ከዚህ በተጨማሪ በአራት የዓለም ዋንጫ እና በሦሥት የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሮች ለቤልጅየም ብሄራዊ ቡድን የተሰለፈው ሉካኩ በእነዚሁ ውድድሮች በዓለም ዋንጫ ስምንት፣ በአውሮፓ ዋንጫ ደግሞ ስድስት ግቦችን በማስቆጠር የሀገሩ የዓለም ዋንጫ እና የአውሮፓ ዋንጫ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው።

ከእነዚህ የስኬት አገልግሎቶቹ በኋላ ግን አሁን ከቱርኩ ፌነርባቼ ክለብ ጋር የሚገኘው የቀድሞው የቼልሲ እና የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ከኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ራሱን በይፋ ማግለሉን አስታውቋል።

ውሳኔውን ይፋ ካደረገ በኋላም ላለፉት 15 ዓመታት ለሀገሬ ባበረከትኩት ነገር ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል ሲል መናገሩን ያሁ ስፖርትስ ዘግቧል።

በኃይሌ አበራ
‎
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_07_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here