አጀማመራቸው ያማረው የባሕርዳር ከነማ ሴቶች!

0
69

የ2019 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ እስካሁን 3 መርሃ ግብሮችን አካሂዷል።በእነዚህ ጨዋታዎች የባህርዳር ከነማ ሴቶች ያስመዘገቡት ውጤት ካለፉት አመታት ጋር ሲነፃፀር መልካም የሚባል ነው።ሁለቱን በድል ሲወጡ አንድ ብቻ ተሸንፈዋል ፡፡

ይህ ውጤት የቡድኑ የማሸነፍ ስነልቦና እያደገ መምጣቱን ማሳያ ነው ብለዋል የቡድኑ አሰልጣኝ እንዳወቀ አጥናፉ እና ቡድኑ ሁለት ጨዋታዎችን ሲያሸንፍ ሁለት ግብ ያስቆጠረችው ወርቅነሽ መሰለ፡፡

የግዮን ንግስቶቹ በአራተኛ ሳምንት ሜዳቸው ላይ ከአዳማ ከተማ ጋር ይጫዎታሉ፡፡

ሁለቱ ክለቦች ባህርዳር በ6 ነጥብ ሶስተኛ አዳማ በ5 ነጥብ አራተኛ ሆነው እርስ በእርስ የሚገናኙበት ጨዋታ በደረጃው ላይ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ጨዋታ ስለሆነ በሜዳቸው ውጤታቸውን እንደሚያስጠብቁ የቡድኑ አባላት እና አሰልጣኙ እምነታቸውን ገልፀዋል።

በተለይም ደግሞ በሁለቱ ያለፉ ጨዋታዎች መረቧን ያላስደፈረችው የቡድኑ ግብ ጠባቂ ባንቻየሁ ደመላሽ ከተጫዋቾቹ ጋር ያለን መግባባት ቡድኑ እንዲያሸንፍ ከማድረግ በላይ ነው ብላለች።

ባ/ዳር ከተማና አዳማ ከተማ የአራተኛ ሳምንት ጨዋታቸውን የፊታችን እሁድ 9 ሰዓት ላይ በባ/ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ያካሂዳሉ።

በዳናይት ሲሳይ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here