ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 3ኛ ዙር ጨዋታውን ዛሬ ከሜዳው ውጭ ከሞዛምቢክ ጋር አድርጓል።
በጨዋታውም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 1 ለ 0 በማሸነፍ በማጣሪያው የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል።
ማፑቶ ላይ በተካሄደው በዚሁ ጨዋታ ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ 86ኛው ደቂቃ ላይ ከንአን ማርክነህ አስቆጥሯል።
ምድቡን ሴኔጋል በ7 ነጥብ ስትመራ ሞዛምቢክ 4፣ኢትዮጵያና ሱዳን እኩል 3 ነጥብ ይዘዋል።
በ4ኛው ዙር ማጣሪያ ኢትዮጵያ የፊታችን ማክሰኞ በባ/ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ሞዛምቢክን ትገጥማለች።



