አጫጭር ስፖርታዊ መረጃዎች፦

0
108

👉የማንችስተር ዩናይትድ መሪዎች አሠልጣኝ ማይክል ካሪክን ለመተካት እና አዲሱ ዋና አሠልጣኝ ለማድረግ ከሞሪሲዮ ፖቼቲኖ ወኪሎች ጋር ድርድር ጀምረዋል።

ፖቼቲኖም ስምምነት ላይ ከተደረሱ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝነት ሚናቸውን ወዲያውኑ በመልቀቅ የዩናይትድ ኀላፊነትን ለመቀበል ዝግጁ መኾናቸውን ገልጸዋል።

👉የፈረንሳይ እና የባየርን ሙኒክ የክንፍ መስመር ተጫዋች ማይክል ኦሊሴ በጫማው ላይ ‘በዓለም ላይ ምርጡ ኳስ አሻጋሪ’ የሚል ጽሑፍ አስቀርጿል።

ተጫዋቹ በ2026 በሁሉም ውድድሮች 29 ግብ የኾኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል በአውሮፓ ከ5ቱ ታላላቅ ሊጎች ከማንኛውም ተጫዋች በላይ ከፍተኛ ግብ የኾኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል የቻለ ቀዳሚው ተጫዋች መኾን ችሏል።

👉የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ፍሬንኪ ዲ ጆንግ ያልተገባቸው ዝቅተኛ ግምት ከሚሰጣቸው ተጫዋቾች አንዱ መኾኑን ገለጹ።

አሠልጣኙ አክለውም ዲ ጆንግ በቡድን አጋሮቹ እና በአሠልጣኞች ዘንድ ምርጡ አማካይ ተደርጎ እንደሚወሰድ እና በጨዋታ ወቅት በርካታ ታክቲካዊ ችግሮችን በመፍታት እና በማጥቃት በኩል የበላይነትን የሚፈጥር ምሉዕ ተጫዋች መኾኑን ተናግረዋል።

👉ማርክ ኩኩሬያ ሪያል ማድሪድ በአሁኑ ሰዓት በአውሮፓ ውስጥ ምርጡ ቡድን መኾኑን በመግለጽ፣ ቪኒሲየስ ጁኒየር ወደ ቀድሞ ድንቅ ብቃቱ ከተመለሰ ደግሞ ቡድኑን “ማንም ሊገታው የማይችል” እንደሚኾን ለስፔኑ የመገናኛ ብዙኅን ኮፔ ተናግሯል።

👉”ባሎንዶር ማሸነፍ እፈልጋለሁ፤ ማሸነፍ እንደምችልም አምናለሁ” ሲል ሪዮ ንጉሞሃ ተናገረ።

የሊቨርፑል እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የወደፊት ተስፋ የኾነው ወጣቱ አጥቂ ሪዮ ንጉሞሃ የሃሪ ኬን የባሎንዶር ክብር ማሸነፍ ለእንግሊዝ ወጣት ተጫዋቾች ትልቅ መነቃቃትን መፍጠሩን ገልጿል።

በብሔራዊ ቡድን ሥብሥብ ውስጥ ከሃሪ ኬን ጎን ለጎን ልምምድ በማድረግ ላይ የሚገኘው ንጉሞሃ በቀጣይ በግሉ የዓለማችንን ከፍተኛ ክብር የኾነውን ባሎንዶር የማሸነፍ ትልቅ ህልም እንዳለው እና ያንን ማሳካት እንደሚችል ሙሉ እምነት እንዳለው ተናግሯል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ህዳር_03_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here