በዳካር የወጣቶች ኦሊምፒክ ትላንት የአትሌቲክስ ውድድሮች ተጀምረዋል፡፡ ኢትዮጵያም በመጀመሪያው ቀን ያገኘችውን ሜዳልያ ታስቀጥላለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ዛሬም የፍጻሜ እና የማጣሪያ ውድድሮች ይከናወናሉ፡፡ በ 4 የውድድር አይነቶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይፎካካራሉ፡፡
ትላንት በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ በሁለተኛው ምድብ የተወዳደረችው ነፃነት ሰለሞን በቀላሉ ምድቧን 2 ደቂቃ ከ08 ሰከንድ ከ28 ማይክሮ ሰከንድ በማሸነፍ ለፍጻሜ መብቃቷ ይታወሳል፡፡ ምሽት 2 ሰዓት ከ 10 ላይ ለሜዳልያ ስትጠበቅ በምድብ ፉክክሯ ላየ ያሳየችውን
በራስ መተማመን ዛሬ ትደግማለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ለፍጻሜው ካለፉ 9 አትሌቶች መካከል በገባችበት ሰአት ፍጥነት በ8 ሰከንዶች ልዩነት የተቀመጠችው ነጻነት የወርቅ ሜዳልያውን ታመጣለች ተብሎም ተገምቷል፡፡ በ2ሺህ ሜትር መሰናክል ፍጻሜ ኢትዮጵያ በብቸኝነት በጁነዲን
አብዶ ትወከላለች። ውድድሩም 11 ሰዓት ከ46 ላይ የሚጀምር ይሆናል።በ3000 ሜትርና 3000 ሜትር መሰናክል ጥሩ ሰአት ያለው ጁነዲን በ3000 ሜትር መሰንክል ያለውን ልምድ ተጠቅሞ አሸናፊ ለመሆን መሙ ላይ ይሰየማል፡፡ ሌላኛው ኢትዮጵያ ለሜዳልያ የምትጠበቅበት
በሴቶች 3ሺህ ሜትር ፍጻሜ ነው፡፡ ከወራት በፊት አሜሪካ ኢዩጅን ላይ በተደረገው የአለም ወጣቶች ሻምፒዮና በርቀቱ ኢትዮጵያ በዮርዳኖስ ጽጋብና በሽቶ ጉሚ የብርና ነሀስ ሜዳልያ ማምጣቷ ይታወሳል፡፡ 8 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ ከ65 ማየክሮ ሰከንድ ደግሞ የርቀቱ ፈጣን ሰአቷ ነው፡፡ በተጨማሪም ኬንያ ላይ በአፍሪካ ዞን 5 ውድድር ላይ ባለድል ስትሆን ዮርዳኖስ ጽጋብ ዛሬ ከሰአት ሜዳልያውን የመውሰድ ቅድመ ግምት ተሰጥቷታል፡፡ ውድደሩም አመሻሽ 12 ሰዓት ከ03 ሲል ሲጀምር ከ8 አትሌቶች ጋር ትፎካከራለች፡፡ በወንዶች 1500 ሜትር ፍፃሜ ደግሞ
አትሌት ዋቢ ወጂራ ምሽት 1 ሰዓት ከ26 ላይ ውድድሩን ያከናውናል፡፡ በ2ኛው የአፍሪካ ዞን 5 ወጣቶች ኦሊምፒክ የ1500 ሜትር የብር ሜዳሊያ ባለቤት የነበረው ዋቢ ለሌላ ድል ከ10 አትሌቶች ጋር ይፎካከራል፡፡ የወንዶች 800 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ ምሽት 1 ሰዓት ከ 10 ላይ
ሲጀመር አትሌት ዮሚፍ አበበ ኢትዮጵያን ይወክላል፡፡ በ2 ምድብ 18 አትሌቶች በሚፎካከሩበት በዚህ ዘርፍ ዮሚፍ 1 ደቂቃ ከ47 ሰከንድ የግሉን ምርጥ ሰአት ይዞ በምድብ 2 ይገኛል፡፡
ሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



