አበረታች ንጥረነገር የሚጠቀሙ አትሌቶች ለሃገራችን ስምና ዝና ፈተና እየሆኑ ነው፡፡

0
36
በአለም አደባባይ ከፍ ብሎ የተውለበለበው አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅ አሁን ቀይ መብራት በርቶበታል፡፡
በማናጀሮች ውጤት መፈለግ እና በአትሌቶች የገንዘብ ሽሚያ ውስጥ የገባው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አሁን ከከፍታው ወርዶ በአበረታች ንጥረ ነገር ተወሯል፡፡
በሃገራችን አበረታች ንጥረ ነገርን የሚጠቀሙ አትሌቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። በዘንድሮው አመት ብቻ ከ50 የተሻገሩ አትሌቶች በተደረገላቸው ምርመራ የተከለከለ ንጥረ ነገር በመጠቀማቸው ውጤታቸው ተሰርዟል፡፡
በዚህ ሳያበቃ አትሌቶች ህገ ወጥነታቸው ሲረጋገጥ ጥፋታቸውን ለመሸፈን ከ89 በመቶ በላይ ሃሰተኛ የህክምና ማስረጃዎችን እያቀረቡ ነው ብሏል የኢትዩጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መኮነን ይደርሳል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በጉዳዩ ላይ በትኩረት መስራቱ የተጋላጭ አትሌቶችን ቁጥር ከፍ እንዲልም አድርጎታል፡፡
አሁን እየተቀጡ እና እርምጃ እየተወሰደባቸው ያሉት አትሌቶች ብቻ ናቸው በቀጣይ ግን ከአትሌቶች ጀርባ ተደብቀው የአትሌቲክሱ ጠላት የሆኑትን ግለሰቦች በወንጀል እንደሚቀጡም ዋና ዳይሬክተሩ ለአሚኮ ስፖርት ተናግረዋል፡፡
ዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here