ኢትዩጵያ በአፍሪካ የወጣች ኦሎምፒክ የመጀመሪያውን የነሃስ ሜዳሊያ አገኝች፡፡

0
69
በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ በሴኔጋል ዳካር እየተከናወነ በሚገኘው የዓለም ወጣቶች ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን በዉሹ ስፖርት የወከለው ናትናኤል ሀጎስ የነሃስ ሜዳሊያ አግኝቷል፡፡
የ16 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ የውሹ ተወዳዳሪ ናትናኤል ሀጎስ በውሹ ስፖርት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ ወክሎ የመጀመሪያውን የነሃስ ሜዳሊያ በማምጣት ራሱን ከታሪክ መዝገብ ላይ አስፍሯል፡፡
በውድድሩ ቻይና የወርቅ ሜዳሊያ ስትወስድ ኢንዶኔዝያ የብር ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡
ኢትዩጵያ በዚህ የወጣቶች ኦሎምፒክ ውሹን ጨምሮ ቴኳንዶ አትሌቲክስ ውሃ ዋና ብስክሌት ስፓርቶች ላይ ለሜዳልያ ትፎካከራለች።
ዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here