የ32 ዓመቱ ፈርናነዴዝ ከሮማ ድል በኋላ በሰጠው አስተያየት ከካሪክ ጋር ስላላቸው ግንኙነት በሚዲያ የሚወራው ሀሰት ነው ሲል አስተባብሏል።
ከአሰልጣኙ ጋር ጥሩ የሚባል ግንኙነት እዳለ ጠቅሶ ተጠባባቂ ቦታ ላይ የተቀመጠው ጥሩ እንቅስቃሴ ስላላደረገ እንደሆነ ተናግሯል።
በትናንትናው የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ በሮማ ላይ ያስመዘገቡት ድል ከዘጠኝ ጨዋታዎች በኋላ የተገኘ ነው።
በሮማ ላይ የተመዘገበው ድል የአሰልጣኙን ከመባረር ስለመታደጉ የተጠየቀው ፈርናንዴዝ ክለቡ ማሸነፍ ስለሚያስፈልገው እነጂ የማንንም ስራ ለማቆየት እና ከመባረር ለማዳን አይደለም ሲል መልሷል።
ካስፐር ሽማይክል የፈርናንዴዝን ሀሳብ በመደገፍ በሚዲያ የሚወራው ከእውነት አንድ ክፍል ብቻ ነው የሚወራው ይላል።
አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ የውድድር ዓመት ከአስራ ሰባት ጨዋታዎች አስራ ሁለት በማሸነፍ ከሁለት አመት በኋላ ዩናይትድ ወደ ቻምፒየንስ ሊግ እንዲመለስ አድርጎ ነበር።
በዘንድሮው የውድድር ዓመት ነገሮች እንደታሰበው ያልሆነላቸው ካሪክ በፕሪሚየር ሊጉ ካደረጓቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች አንድ ብቻ አሸንፎ አራት አቻ በመለያየት 17ኛ ላይ ተቀምጧል።
በሻምፒዮንስ ሊጉ ደግሞ ከትናንቱ ምሽት አስደናቂ ድል በኋላ ከአራት ጨዋታዎች በሁለቱ ድል በማድረግ ሁለት ተሸንፎ በስድስት ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
መሀሪው አወቀ (የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምሕርት የተግባር ተለማማጅ)
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



