ዛሬ ምሽት በአትሌቲኮ ማድሪድ እና ባየር ሙኒክ መካከል በሚደረገው ተጠባቂ የአራተኛ ዙር የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ላይ የመሀል ሜዳውን በዳኝነት እንዲመሩ የተመረጡት ፈረንሣዊው ዳኛ ፍራንሷ ሌቴክሰዬር ናቸው። ይህ ዳኛ ደግሞ የባየር ሙኒክ መጥፎ እድል እንደሆነ የክለቡ ደጋፊዎች እየገለፁ ይገኛሉ ።
ከዚህ ቀደም በርካታ ታላላቅ ጨዋታዎችን በመምራት ልምድ ማካበት የቻሉት የ37 አመቱ ፈረንሳዊው የመሀል ዳኛ ከዚህ ቀደም የጀርመኑ ክለብ ያደረጋቸውን ሶስት ጨዋታዎች መምራት ችለዋል። በነዚህ ሶስቱንም ጨዋታዎች በሽንፈት ያጠናቀቁት ባየር ሙኒኮች ምሽትም ተመሳሳይ እጣ ፋንታ እንዳይገጥማቸው ስጋት ላይ ናቸው ።
በ2025 የአለም የክለቦች ዋንጫ ጨዋታ ባየር ሙኒኮች በቤንፊካ 1ለዐ ሲሸነፍ ፤ በ2023/24 የቻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ላይ በላዚዮ 1ለ0 ሲረቱ እንዲሁም በ2024/25 በቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ላይ በፌኖርድ 3ለ0 ሲሸነፉ የመሀል ሜዳውን የመሩት እኒህ ፈረንሣዊው ዳኛ ናቸው።
ዛሬ ምሽት በዋንዳሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም በሚደረገው ተጠባቂ ጨዋታ ላይ ባቫሪያኖቹ እንደ ቀድሞ መጥፎ እድል ይገጥማቸዋል ወይስ አዲስ ታሪክ ያስመዘግቡ ይሆን የሚለው በጉጉት ይጠበቃል ።
የጋዜጠኝነት የተግባር ተለማማጅ ( ኤርምያስ ገረመው)
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



