“ባሎንዶሬን በቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ እቀይራለው ” ሀሪ ኬን

0
37
እንግሊዛዊው አጥቂ ሀሪ ኬን ባየርን ሙኒክ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን እንዲያነሳ መርዳት የሚችል ከሆነ ያሸነፈውን የባሎንዶር ሽልማት ለመለወጥ ፍቃደኛ መሆኑን ተናገረ ።
የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አምበል እና የባየርን ሙኒኩ አጥቂ ሃሪ ኬን ኪሊያን ምባፔን እና ላሚን ያማልን በመብለጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል።
ኬን በ2025-26 የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች 73 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን በእንግሊዛዊያን ተጫዋቾች ታሪክ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።
ሆኖም ተጫዋቹ አሁን ዋና ትኩረቱ ከባየርን ሙኒክ ጋር የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግን ማሸነፍ እንደሆነ ገልጿል።
የባሎንዶርን ማሸነፍ የሕይወቴ ትልቅ ስኬት ቢሆንም፣ ከቡድኔ ጋር የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ማንሳት የበለጠ አስደናቂ ስሜት አለው ያለው ኬን ሁለቱንም የማሸነፍ ዕድል ከፊቱ እንዳለ ገልጿል።
ሀሪ ኬን በባየርን ሙኒክ የሚያቆየውን ዉል ለማደስ ንግግር ላይ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
የጋዜጠኝነት የተግባር ተለማማጅ (ሀሚድ አብደላ)
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here