የአዉሮፓ ቻምፒዎንስ ሊግ አራተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ መደረግ ይጀምራሉ።

0
62
‎‎ከተጠባቂ ጨዋታዎች መካከልም በአውሮፓ ቻምፒዎንስ ሊግ የዘንድሮ ሶስቱንም ጨዋታዎች በማሸነፈ 9 ነጥብ ያለው አስቶን ቪላ ከሜዳዉ ውጪ ከሀንሲ ፍሊኩ ባርሴሎና ጋር ይጫወታል::
‎
‎ባርሴሎናዎች የውድድሩ የተከታታይ አመት ባለክብር በሆነው ፓሪሴንት ዥርሜ የደረሰበትን የ4 ለ 2 ሽንፈት በድል ለመካስ የሚታትርበት ጨዋታ ነው። የአስቶን ቪላው አሰልጣኝ ኡናይ ኢምሪ 55ኛ አመት የልደት ቀናቸውን በድል ማጀብም ይፈልጋሉ።
በመሆኑም በጨዋታው ከፍተኛ ፉክክር ይጠበቃል::
‎
‎በሌላ በኩል አትሌቲኮ ማድሪድ የጀርመኑን ሀያል ክለብ ባየር ሙኒክን በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም ያስተናግዳል።
ሁለቱ ቡድኖች የዘንድሮ የመድረኩ ጅማሯቸው በሚጠበቀው ልክ አይደለም። ‎ባየር ሙኒክ ባለፉት ሶስት የአዎሮፓ ቻምፒዎንስ ሊግ ጨዋታዎች መካከል በአንዱ አሸንፎ በሁለቱ ነጥብን በመጋራት 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል::
በአንፃሩ አትሌቲኮ ማድሪድ አንድ ጨዋታን አሸንፎ በአንዱ ሽንፈትን አስተናግዶ እንዲሁም አንድ ጊዜ አቻ የወጣ ሲሆን በ16 ደረጃ ላይ ይገኛል::
‎
‎ሌላው ተጠባቂ ጨዋታ ለተከታታይ ጊዜ በአውሮፓ ቻምፒዎንስ ሊግ መድረክ ላይ የነገሰውና ሊጉን በ9 ነጥብ እየመራው የሚገኘው ፓሪሰንት ጀርመን ከስፔኑ ቪያሪያል ጋር ከሜዳው ዉጪ ጨዋታውን ያደርጋል::
‎
‎በሊውስ ኢንሪኬ እየተመሩ አስገራሚ ብቃት እያሳዩ ያሉት ፓሪሰንት ጀርሜዎች ከባድ ፈተና ከቪያሪያል ይጠብቃቸዋል:: መሪነታቸውን ለማስጠበቅም ሙሉ 3 ነጥብ ለማሳካት ይጥራሉ። ነገር ግን 4ሁነኛ ተጨዋቾች ማለትም ደምበሌ፤ ክቫርስኬልያ ኑኖ ሜንዴዝ እና ማርኪንሆስ ጉዳት ላይ መሆናቸው የኢንሪኬን የታክቲክ ነፃነት ይነፍጋል።
‎
‎በሌላ በኩል ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሮማ ይጫወታሉ:: ‎በተደጋጋሚ ሽንፈትን እያስተናገዱ የሚገኙት በአሰልጣኝ ማይክል ካሪክ የሚመሩት ቀያይ ሰይጣኖቹ የጣሊያኑን ክለብ ሮማ በሜዳቸው ኦልድትራፎርድ ያስተናግዳሉ:: ሮማ በሴሪኤውም ይሁን በአውሮፓ መድረክ ካለፉት አመታት አቋሙ በተሻለ ደረጃ ይገኛል።
‎
‎የጣሊያኑ ሀያል ክለብ ኢንተር ሚላን ከፌይኖረድ ጋር ይጫዎታል:: በአሰልጣኝ ክርስቲያን ኪቩ የሚመራዉ ኢንተር ሚላን ከ 3 ጨዋታ በሁለቱ ተሸንፎ 20ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል:: ካለበት የደረጃ ሰንጠረዥም ከፍ ለማለት ከሜዳዉ ውጪ አቅንቶ ከፌይኖርድ ጋር ይገናኛል:: በሌሎች
መርሀግብሮች ቦዶ ግሊምት ከሊል ጋር የሚገናኙ ሲሆን ላስክ ስሎቫን በራቲስላቭ ጋረ ይጫዎታል። እነዚህ ጨዋታዎች ምሽት 5:00 ሰዓት ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ሲሆኑቀደም ብሎ ምሽት 2:45 ላይ ደሞ ‎ጋላታሳራይ ከስቱትጋርት እንዲሁም ሻክታር ከስፖርቲንግ ጋር ይካሄዳሉ::
‎
የጋዜጠኝነት ትምህርት የተግባር ተለማማጅ (ዮሴፍ የኔዓለም)
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here