በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት መሪው ማንቸስተር ሲቲ በብራይተን መሸነፉን ተከትሎ፣ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አርሰናል የሊጉን መሪነት የመረከብ ወርቃማ ዕድል የሚያገኝበትን ጨዋታ ያደርጋል። ጥያቄው ይህን ዕድል ያባክናል ወይስ ይጠቀምበታል የሚለው ይኾናል።
ሊቨርፑል እና አርሰናል የሚያደርጉት ይህ ተጠባቂ ጨዋታ በአንፊልድ ምሽት 1፡30 ላይ ይካሄዳል።
ባለሜዳው ሊቨርፑል በሳምንቱ አጋማሽ በካራባዎ ዋንጫ ቼልሲን በመለያ ምት ማሸነፉ እና በሊጉም ብሬንትፎርድን እና ብራይተንን በተከታታይ ማሸነፉ በጥሩ መነቃቃት ላይ የሚገኝ በመኾኑ ለአርሰናል ፈተና ይሆናል።
ሊቨርፑል አርሰናልን ካሸነፈ እ.አ.አ ከ2009 በኋላ ከማንቸስተር ዩናይትድ በመቀጠል በሊጉ ታሪክ ሦሥት ምርጥ አራት ውስጥ የተቀመጡ ቡድኖችን በተከታታይ ያሸነፈ ሁለተኛው ክለብ በመኾን አዲስ ታሪክ ይጽፋል።
አሌክሳንደር ኢሳክ ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን በማስቆጠር ጥሩ ወቅታዊ አቋም ላይ በመኾኑ ለቡድኑ እንደመልካም ዕድል ይቆጠራል።
ሁጎ ኤኪቲኬ፣ ኮኖር ብራድሌይ፣ ጄሬሚ ፍሪምፖንግ እና ጆቫኒ ሌኦኒ በጉዳት ከጨዋታው ውጪ መኾናቸው ሥብሥቡ የተሻለ ውጤት እንዳያገኝ እንቅፋት እንደሚኾን ያጠበቃል።
በሚኬል አርቴታ የሚመራው አርሰናል በሳምንቱ አጋማሽ በካራባዎ ዋንጫ በፍሊትዉድ ታውን ተሸንፎ መሰናበቱ ለዛሬ ጨዋታ ከስነልቦና አንጻር ተጽኖ እንደሚኖረው ነው የሚጠበቀው።
መድፈኞቹ እ.አ.አ 2012/13 ጀምሮ ባሉት ያለፉት 14 ዓመታት በአንፊልድ ባደረጓቸው የፕሪሚየር ሊግ ጉዞዎች 5 አቻ እና 8 ሽንፈቶችን በማስመዝገብ አንድም ድል አለማስመዝገባቸው ለቡድኑ ሜዳው ምን ያክል አስቸጋሪ እንደኾነ ጠቋሚ ነው።
ቡካዮ ሳካ በጉዳት፣ ወጣቱ ማክስ ዳውማን ደግሞ በቅጣት አይሰለፉም።
አርሰናል አሸንፎ ከሜዳው ውጪ 300ኛ ድሉን በማስመዝገብ መሪነቱን ይረከባል? ወይስ ሊቨርፑሎች በአንፊልድ ያላቸውን የረጅም ጊዜ የበላይነት ያስጠብቃሉ?
እናንተስ ማን አሸንፎ ታሪክ ይጽፋል ግምታችሁን አስቀምጡ።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_22_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



