አዲስ አበባ: ጥቅምት 21/2019(አሚኮ) ከአመታት በኋላ የእግር ኳስ ፀሀይ በባህርዳር አለም አቀፍ ስቴድየም ወጥቷል።

0
132

“ይናጋ ይናጋ ዘንባባው ይናጋ ፣ ፋሲል ከነማ የጎንደር አርማ”

የፋሲል ከነማና የባህር ዳር ከተማ ጨዋታ በባህርዳር ሊደምቅ የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ እንገኛለን። የተለያዩ አካባቢዎች ውብ ደጋፊዎች በዕለተ ቅዳሜ የታላቁ ባህር ዳር ስታድየም ሞገስ ኾነዋል።

ከጨዋታ እና ሶስት ነጥቡ በላይ ውብ ደጋፊነት የሚደምቅበት፤ ወንድማማችነት በተግባር እና በጨዋነት የሚገለጥበት ውሀ ሰማያዊ ከነጭ እና ቀይ ከነጭ ጋር የተዋሀዱ መለያዎች ደማቅ ድባብ የሚፈጥሩበት ተናፋቂ ጨዋታ።

አንዳንዶቹ ወንድማማቾች ደርቢ ይሉታል፤ ሌሎች የጣና ደርቢ እያሉ ይጠሩታል። በደጋፊዎች በተለየ ይናፈቃል።

ያኔ በሌሎች ስቴድየሞች ተዘዋውረው ከጎናቸው የነበሩ ልባቸው አብሮ የተንንከራተተ ተመስጋኝ ደጋፊዎች ዛሬ ቀን ወጥቶላቸዋል።

ከሚወዷቸው ክለቦች ጎን ኾነው “ይሰማል!” እያሉ የየክለቦቻቸውን አርማ አንግበው በክብር ሊያበረታቱ በጥፍራቸው ቆመዋል።ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰዓት በባህርዳር ስታድየም- ባህር ዳር ከነማ ከ ፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here