ዛሬ ባሕር ዳር እና የባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም ይደምቃሉ።
የወንድማማቾቹ ደርቢ ጨዋታ ደጋፊዎች የሚያሳዩት ትዕይንት ደግሞ የጨዋታው ትልቅ ሞገስ ነው።
ይህ የደጋፊዎች ሀብታም የኾነው የደርቢ ጨዋታ አንዱ ሌላውን አሸንፎ ለመውጣት ብቻ ሳይኾን የኳስ እና የእርስ በእርስ መዋደድ ማሳያም ነው።
ይህ የደርቢ ጨዋታ ሰዓታት በቀሩበት በአሁኑ ወቅት በባሕር ዳር በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎችም ትኬቱ እየተሸጠ ይገኛል።
ከጨዋታው አስቀድሞ ታዲያ የሁለቱ ክለቦች አሠልጣኞች በሰጡት ሃሳብ እንዳሉት ደጋፊዎቻችን የጨዋታው ጉልበታችን ናቸው ብለዋል።
የባሕር ዳር ከተማ (የጣና ሞገዶቹ) አሠልጣኝ ደግአረገ ይግዛው እንዳሉት 2015 ለመጨረሻ ጊዜ ከፋሲል ከነማ ጋር የተገናኘነው በአምስተኛው ሳምንት በባሕር ዳር ስታዲየም ነበር፤ አሁንም ታሪክ ራሱን ደግሞ በአምስተኛው ሳምንት ከፋሲል ከነማ ጋር እዚሁ ከፋሲል ከነማ ጋር መገናኘታችን እጅግ የሚገርም አጋጣሚ ነው ብለዋል።
ከ90 ደቂቃ ጨዋታ በኋላ ደግሞ በስፖርታዊ ጨዋነት በመልካም ሁኔታ ደጋፊዎቻችን የውድድሩ ድምቀት ሁነው እንደሚታዩ ምኞቴ የጸና ነው ሲሉም ጠንክረው እንደሚጫወቱ ነው የጠቆሙት። ደጋፊዎችም በሜዳ ተገኝተው ቡድናቸውን እንዲያበረታቱ ጥሪ አቅርበዋል።
ሌላው የፋሲል ከነማ (አጼዎቹ ) አሠልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዎርጊስ ጨዋታው ሞቅ ያለ ከሜዳም ውጭ የድጋፍ አሠጣጡ የተለየ እንደሚኾን እንጠብቃለን ነው ያሉት።
እስካሁን ባሕር ዳር ከሦሥቱ ሁለቱን አሸንፏል ፋሲል ከነማ ደግሞ እስካሁን ወደ አሸናፊነት ያልመጣ በመኾኑ ይህን ጨዋታ በደጋፊው ታጅበን ለማሸነፍ ዝግጁ ነን ብለዋል።
ምንም እንኳን ባለፉት ሳምንታት በሊጉ ባለው ውጤት ልዩነት ቢኖርም ደርቢ ሲኾን ልዩ እና የተሻለ ይኾናል ነው ያሉት።
የደርቢ ጨዋታ የራሱ ፉክክር እና ለዛ አለው። ብዙ ደርቢዎችን እዚህ ባሕር ዳር አይቻለው ልዩ ስፖርታዊ ጨዋነት የተሞላበት ነበር። ዛሬም ደርቢዎች ምን ያክል ጠንካራ ፉክክር እንዳለባቸው እና ውበቱን ለዓለም የምናሳይበት ይኾናል ሲሉ ጨዋታውን አሸንፈው ለመውጣት የሚችሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ነው የተናገሩት።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_21_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



