ከአመታት በኋላ የእግር ኳስ ፀሀይ በባህርዳር አለም አቀፍ ስቴድየም ወጥቷል።
ወንድማማቾቹ በታላቁ የጣና ሀይቅ የሚለዩት የጎንደርና ባህርዳር ከተሞች ክለቦች ደርቪ፤ የፋሲል ከነማና የባህር ዳር ከተማ ጨዋታ በባህርዳር ሊደምቅ ቀኑ ደረሰ። የተለያዩ አካባቢዎች ውብ ደጋፊዎች በዕለተ ቅዳሜ የታላቁ ባህር ዳር ስታድየም ሞገስ ይሆናሉ።
ከጨዋታ እና ሶስት ነጥቡ በላይ ውብ ደጋፊነት የሚደምቅበት፤ ወንድማማችነት በተግባር እና በጨዋነት የሚገለጥበት ውሀ ሰማያዊ ከነጭ እና ቀይ ከነጭ ጋር የተዋሀዱ መለያዎች ደማቅ ድባብ የሚፈጥሩበት ተናፋቂ ጨዋታ።
አንዳንዶቹ ወንድማማቾች ደርቪ ይሉታል፤ ሌሎች የጣና ደርቪ እያሉ ይጠሩታል። በደጋፊዎች በተለየ ይናፈቃል።
ያኔ በሌሎች ስቴድየሞች ተዘዋውረው ከጎናቸው የነበሩ ልባቸው አብሮ የተንንከራተተ ተመስጋኝ ደጋፊዎች ዛሬ ቀን ወጥቶቸዋል።
ከሚወዷቸው ክለቦች ጎን ሆነው ይሰማል እያሉ የየክለቦቻቸውን አርማ አንግበው በክብር ሊያበረታቱ በጥፍራቸው ቆመዋል።
እኛም የዚህ ትእይንት አካል ለመሆን ያን ቀን እለተ ቅዳሜ 9 ሰአት እየጠበቅን ነው።
በዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



