በጣልያን ሴሪ ኤ 9ኛ ሳምንት የትናንት ጨዋታዎች ኢንተር ሚላን እና ናፓሊ ድል ሲያደርጉ ኤስ ሚላን እና ጅቬንቱስ ተሸንፈዋል።

0
62
የአምናው ሻምፒዮን ኢንተር ሚላን ከሜዳው ውጭ ቬንሽያን በጋበዘበት ጨዋታ ተፈትኖ አምሽቷል።
መደበኛ የጨዋታ ጊዜ ሊጠናቀቅ 10 ደቂቃ ሲቀር ድረስ ጨዋታው ግብ አልተቆጠረበትም። ሆኖም በቀሪ ደቂቃዎች የቬንሽያ ተጨዋቾች ሞሪኖ እና ሀልሀል በራሳቸው ግብ አስቆጥረው ኢንተር 2ለ0 አሸንፏል።
ናፓሊ ከሜዳው ውጭ ሞንዛን 4ለ1 ረቷል። ለኔፕልሱ ክለብ ሆይሉንድ ፣ ፓሊታኖ ፣ ራፋ ማሪን እና ዲብሩይነ አስቆጥረዋል።
ኤስ ሚላን በሳንሴሮ በቦሎኛ ተሸንፏል። 6 ግቦች በተቆጠሩበት ጨዋታ የቦሎኛው ባንጉላ ሀትሪክ ሰርቷል። ለሚላን ሲሴ 2 ግብ ቢያስቆጥርም ሚላን 4ለ2 ከመሸነፍ አልዳነም።
ጅቬንቱስ ደግሞ በጅንዋ 2ለዐ ተረቷል። የፓርማና የዩድንዜ ጨዋታ ያለ ጎል ተጠናቋል።
ሴሪ ኤውን ላዚዮ እና ኢንተር ሚላን በእኩል 25 ነጥብ ይመራሉ።
መለሰ ግዛቸው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here