“ጃኦ ፔድሮን እንናፍቀዋለን “ ዣቪ አሎንሶ

0
79
ቼልሲ አጥቂውን ጃኦ ፔድሮን በጉዳት ማጣቱን ተከትሎ በአጥቂ ክፍሉ ላይ መሳሳት ገጥሞታል።
ብራዚላዊው ተጫዋች በዚህ የውድድር ዘመን 5 ግቦችን አስቆጥሮ 3 ግብ የሆኑ ኳሶችን አቀብሏል።
ተጫዋቹ ባልነበረባቸው የብሬንትፎርድ እና የቶተንሀም የኘሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የዣቪ አሎንሶ ቡድን ግብ ለማግኘት መቸገሩ የተጫዋቹን አስፈላጊነት አስመስክሯል።
ዛሬ መግለጫ የሰጡት ዦቪ አሎንሶ ጃኦ ፔድሮ የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች ነው ያሉ ሲሆን በእርግጠኝነት እንናፍቀዋለን ሲሉም ተናግረዋል።
የፔድሮን ክፍተትም በዊልቤክ እና ሌሎች ተጫዋቾች እንደሚሞሉት ጠቁመዋል።
ጃኦ ፔድሮ የታፋ ጉዳት የገጠመው ሲሆን ለጥቂት ሳምንታት ከሜዳ ይርቃል።
ቼልሲ በእንግሊዝ ሊግ ዋንጫ ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት አንፊልድ ላይ ከሊቨርፑል ጋር ይጫወታል።
የጋዜጠኝነት የተግባር ተለማማጅ (ሀሚድ አብደላ)
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here