ሁለተኛ ዙር ማጣርያ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው ቡድኑ ዛሬ 10:00 በድሬዳዋ ስታድየም የመልስ ጨዋታ ከሩዋንዳ ጋር ያደርጋል።
የመጀመርያው ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጭ ኪጋሊ ላይ አድርገው 1-0 ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው።
ለዛሬው ጨዋታ ደግሞ ከሀገር ውጭ በአሜሪካ የምትጫወተው ሎዛ አበራ ቡድኑን ተቀላቅላለች። የበለጠ አቅም እንደምትሆን ይጠበቃል።
የዚህ ማጣሪያ የደርሶ መልስ አሸናፊ በ3ኛ ዙር ከቦትስዋና እና ታንዛንያ አሸናፊ ጋር ይጫወታል።
በመለሰ ግዛቸው
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_03_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



