ዛሬ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ሲደረጉ ከባድ የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ፤ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ በዲያጎ ሲሚዮኔ ከሚመራው ጠንካራው አትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ተጠባቂ ጨዋታውን ያደርጋል።
ቀያይ ሰይጣኖቹ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ሳይጨምር ከስፔኑ ተጋጣሚያቸው ጋር ባደረጓቸው አራት ጨዋታዎች በአንዱም ድል ቀንቷቸው አያውቅም። አትሌቲኮዎች በሁለቱ ሲያሸንፉ፣ ሁለቱ በአቻ ውጤት ተጠናቅቀዋል።
ዩናይትድ በአውሮፓ ውድድሮች አምስት ጨዋታዎችን አድርጎ ማሸነፍ ያልቻለው ሌላኛውን የስፔን ክለብ ሲቪያን ሲኾን፣ ዛሬ ከአትሌቲኮ ጋር ማሸነፍ ካልቻለ ከሌላኛው የስፔን ክለብ ጋር ያለምንም ድል አምስተኛው ጨዋታ ይሆናል።
አትሌቲኮ ማድሪድ ከእንግሊዝ ክለቦች ጋር ባደረጋቸው 15 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በሁለት አጋጣሚዎች ብቻ ሲኾን፣ በ10 ጨዋታዎች ግን ሽንፈት አስተናግዷል።
ሁለቱ ክለቦች በየሊጎቻቸው ፈጽሞ የተለያየ የውጤት ጎዳና ላይ ይገኛሉ። አትሌቲኮ ማድሪድ በሀገር ውስጥ ውድድሮቻቸው ስድስት ድሎችን በማስመዝገብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ ግን አንድ ድል ብቻ በማስመዝገብ በሊጉ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ከጨዋታው አስቀድሞ በወጡ ትንበያዎች አትሌቲኮ ማድሪድ 46 በመቶ የማሸነፍ ግምት ሲያገኝ፣ ማንችስተር ዩናይትድ 30 በመቶ ዕድል ተሰጥቶታል።
በማንችስተር ዩናይትድ በኩል ኮቢ ማይኑ፣ ሉክ ሻው፣ ቤንጃሚን ሼሽኮ፣ ፓትሪክ ዶርጉ እና ኑሳይር ማዝራዊ በጉዳት ምክንያት ከሥብሥቡ ውጪ ኾነዋል።
በአትሌቲኮ ማድሪድ በኩል ደግሞ በሳምንቱ መጨረሻ ፓብሎ ባሪዮስ እና አሌክሳንደር ሶርሎ ወደ ሜዳ መመለሳቸውን ተከትሎ ከጉዳት ነፃ በኾነ ሙሉ ሥብሥብ ለጨዋታው ይቀርባሉ።
ይህ እጅግ አጓጊ የሻምፒዮንስ ሊግ ፍልሚያ ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።
በሌሎች የሻምፒዎንስ ሊግ ጨዋታዎች
አርሰናል ከ ሊል
ጋላታሳራይ ከ ባርሴሎና
ኢንተር ሚላን ከ ክለብ ብሩጅ
አርቢ ሌፕዚግ ከ ፒኤስቪ
ቪኪንግ ከ ባየር ሙኒክ
ቪያሪያል ከ ናፖሊ ምሽት 4፡00 ጨዋታቸውን ሲያደርጉ
ሌንስ ከ ስፖርቲንግ ሲፒ እና
ሳባህ ኤፍኬ ከ ስላቪያ ምሽት 1፡45 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



