የጣና ሞገዶቹ አመቱን በድል ጀምረዋል።

0
41
ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ ቀጥሎ ተካሂዷል።
ከሜዳቸው ውጭ ወደ ሆሳእና ተጉዘው በአብዮ ኤርሳሞ ስታዲየም ከሀድያ ሆሳእና ጋር የተጫወቱት ባህርዳር ከተማዎች የውድድር አመቱን የመጀመሪያ ጨዋታ በድል አሀዱ ብለዋል።
በሙከራ እና ወደ ግብ በመድረስ ብልጫ የነበረው የደግአረገ ይግዛው ስብስብ ባህርዳር ከነማ በፈጣኑ አጥቂ አንተነህ ተፈራ አማካኝነት የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ሰከንዶች ሲቀሩት ባስቆጠራት ግብ ከጨዋታው ሶስት ነጥብ ወስዷል።
ሀድያ ሆሳእና በጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ግብ ለማስቆጠር ያደረጉት ጥረት በግብ ጠባቂው ፔፔ ሰይዶ ጥረት እና ተጫዋቾች ያገኙትን እድል አለመጠቀማቸው ሳይሳካላቸው ቀርቷል።
ሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ላይ ባለሜዳው ሀዋሳ ከተማ መቻልን በደጋፊው ፊት ገጥሞ ተሸንፏል።
ለመቻል ቢኒያም ተክሉ የማሸነፊያ ግቧን አስቆጥሯል።
አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ የተደረገው የኢትዮጵያ ቡና እና ሸገር ከተማ ጨዋታ በሸገር ከተማ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
የሸገር ከተማን አሸናፊ ያደረገች ግብ ካሌብ በየነ አስቆጥሯል።
በዳናይት ሲሳይ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here