ቪኒሲየስ ጁኒየር ለኤል ክላሲኮ መሰለፉ አጠራጣሪ ኾኗል።

0
41
የሪያል ማድሪዱ አጥቂ ቪኒሲየስ ጁኒየር ቪያሪያልን 1 ለ 0 ባሸነፉበት የላሊጋ ጨዋታ ቀይ ካርድ ከተመለከተ በኋላ በሚቀጥለው ሳምንት ከባርሴሎና ጋር በሚደረገው ታላቁ ኤል ክላሲኮ ጨዋታ ላይ የመሰለፍ እድሉ አጠራጣሪ ኾኗል።
ቪኒሲየስ በሁለተኛው አጋማሽ ግብ አግብቶ የነበረ ቢኾንም የቪያሪያሉን ተከላካይ ናታን ሳሊባን ፀጉር በመሳቡ ምክንያት በቪኤአር ታይቶ የገባው ግብ ተሰርዞ በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
የጨዋታው ዳኛ ኢሲድሮ ዲያዝ ቪኒሲየስ ከሜዳ ከተሰናበተ በኋላም በከፍተኛ ድምጽ እየጮኸ፣ “ቁጣና የጠብ አጫሪነት ባህሪ በማሳየት ተቃውሞውን ሲያሰማ ነበር” ብለው ሪፖርት አድርገዋል።
እንደ ኮፕ ዘገባ በዳኛው ሪፖርት ምክንያት የ3 ጨዋታዎች እገዳ ሊጣልበት ይችላል ነው ያለው። ይግባኝ ተጠይቆ ቅጣቱ ወደ 2 ጨዋታ እንኳን ቢቀነስ ቪኒሲየስ ከሴቪያ እና ከባርሴሎና ጋር የሚደረጉትን የላሊጋ ጨዋታዎች ያመልጡታል ተብሏል።
ሪያል ማድሪድ ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ ለማለት እና የቅጣት መጠኑን ለማስቀነስ ወይም ለማስሰረዝ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here