ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ቶተንሃም የዛሬው ተጠባቂ ጨዋታ።

0
24

ዛሬ ምሽት 1፡30 ኦልድ ትራፎርድ ላይ በሚደረገው የስድስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ በማይክል ካሪክ እየተመራ በሮቤርቶ ዴ ዜርቢ የሚመራውን ቶተንሃም ሆትስያስን ያስተናግዳል።

ማንቸስተር ዩናይትድ አምስት ነጥብ ያለው ሲኾን 12ኛ ደረጃ ተቀምጧል። ቡድኑ ባለፉት አራት የሀገር ውስጥ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

ቶተንሃም በበኩሉ እስካሁን ድል አላስመዘገበም የደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይም ይገኛል።

ከተጫዋቾች አንጻር ዩናይትድ ፓትሪክ ዶርጉ፣ ቤንጃሚን ሼሽኮ፣ ኑሳይር ማዝራዊ፣ ማኑኤል ኡጋርቴ እና ማትያስ ዴ ሊክት በጉዳት አይሰለፉም፤ ካርሎስ ባሌባ፣ አማድ ዲያሎ፣ ማርከስ ራሽፎርድ እና ኮቢ ሜይኑ ግን በሥብሥቡ ውስጥ ተካትተዋል።

በቶተንሃም በኩል ዣቪ ሲሞንስ፣ ፔድሮ ፖሮ እና ሚካሂሎ ሙድሪክ ሲጎዱ፣ ሚኪ ቫን ዴ ቪን አገግሟል።

ሌሎች መርሐ ግብሮችም ሲቀጥሉ ቀን 8፡30 ላይ አርሰናል ከ ሊድስ ዩናይትድ በኢሚሬትስ ሲጫዎቱ ቀን 11፡00 አስቶን ቪላ ከ ብሬንትፎርድ፣ ቼልሲ ከ ቦርንማውዝ፣ ኢፕስዊች ከ ፉልሃም፣ ሰንደርላንድ ከ ብራይተን በተመሳሳይ ሰዓት ይጫዎታሉ።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_30_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here