የስፔን ብሔራዊ ቡድን በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ እያስመዘገበ ያለውን አስደናቂ የበላይነት አጠናክሮ በመቀጠል ተከታታይ ያለመሸነፍ ጉዞውን ወደ 42 ጨዋታዎች በማሳደግ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።
በአሰልጣኝ ሉዊስ ዲ ላ ፎንቴ የሚመራው የ«ላ ሮሃ» ስብስብ በአውሮፖ ኔሽንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ከሜዳው ውጭ ከክሮኤሺያ ጋር ባደረገው ተጠባቂ ፍልሚያ 2 ለ 1 በኾነ ውጤት በማሸነፍ አሸንፏል።
በዚህ ጨዋታ ላይ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው አማካዩ ሚኬል ሜሪኖ በ61ኛው እና በ89ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራቸው ሁለት ግቦች የስፔንን ማሸነፍ ያረጋገጡ ሲኾን ቡድኑ በምድብ 3 በ12 ነጥብ መሪነቱን በማጠናከር ወደ ሩብ ፍጻሜው እንዲያልፍ አስችሎታል።
የክሮኤሺያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ጠንካራ ግፊት ቢያደርግም፣ በጨዋታው ማጠቃለያ አካባቢ የተቆጠረችው የሜሪኖ ግብ ስፔኖች ያለመሸነፍ ጉዟቸውን አስጠብቀው እንዲወጡ አድርጓቸዋል።
ከ2024 ጀምሮ ሽንፈት ምን እንደኾነ ያላወቀው የስፔን ብሔራዊ ቡድን፣ በዚህ ረጅም የ42 ጨዋታዎች ጉዞው ወቅት የዩሮ 2024 ዋንጫን በታላቅ የበላይነት ከመቀዳጀቱም በላይ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የማይደፈር ሥብሥብ መኾኑን አስመስክሯል።
የአሰልጣኝ ዲ ላ ፎንቴ ስልታዊ ጥበብ እ፤የታዳጊዎች ብቃት እንዲሁም የልምድ ባለቤቶች ጥምረት ቡድኑን ወደ አዲስ የክብር ማዕረግ ያሸጋገረው ሲኾን አሁን የተመዘገበው የ42 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ታሪክም በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ላይ በወርቃማ ቀለም ተፅፏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



