ማንቼስተር ዩናይትድ የጄጄ ጋብሬል ፍቅር ሊለቀው አልቻለም።

0
17
ጄጄ ጋብሬል የ ማንቼስተር ዩናይትድ ይፋዊ የቡድን ፎቶ ላይ ቢካተትም ክለቡን የመልቀቅ ፍላጎቱ አልተቀየረም።
የ16 ዓመቱ ታዳጊ አጥቂ ጄጄ ጋብሬል በይፋ በተለቀቀው የማንቼስተር ዩናይትድ ይፋዊ የቡድን ፎቶ ላይ ቢታይም፣ ከክለቡ ጋር ያለው ውጥረት አልበረደም፤ ከኦልድ ትራፎርድ ለመልቀቅ የሚያደርገው ጥረትም ቀጥሏል።
ፎቶው የተነሳው መስከረም 8 ቀን ሲኾን፣ ይህም ተጫዋቹ ለክለቡ የመጨረሻ ጨዋታውን ከማድረጉ እና የመልቀቅ ፍላጎቱን ይፋ ከማድረጉ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ እንደነበር ተገልጿል።
ማንቼስተር ዩናይትድ አሁንም ችግሩን ለመፍታት ተደጋጋሚ ጥረቶችን ቢያደርግም እስካሁን ውጤት አላገኘም።
እንደ ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና ያሉ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ተጫዋቹን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸው የተገለጸ ሲኾን የአውሮፓ ኅብረት ፓስፖርት ማግኘቱ ወደ አህጉሩ የሚያደርገውን ዝውውር ያቀልለዋል ተብሏል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ዩናይትድ በበኩሉ ሕግን የጣሰ ዝውውር ወይም ማታለል በኤጀንቶች ወይም በክለቦች በኩል ከተፈጸመ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here