«በኳስ ሂወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ እፍረት ተሰማኝ»

0
11
የክሮሺያ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሉካ ሞድሪች ቡድናቸው በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ በእንግሊዝ 7 ለ 0 በኾነ ሰፊ የግብ ልዩነት ከተሸነፈ በኋላ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እና እፍረት ገልጿል።
ሞድሪች በብሔራዊ ቡድን ውስጥ ለ20 ዓመታት አሳልፌአለሁ፤ ነገር ግን ከጨዋታ በኋላ እፍረት ሲሰማኝ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜዬ ነው ሲል ተናግሯል።
በጨዋታ ልትሸነፍ ወይም ከአንተ የተሻለ ብቃት ካለው ቡድን ጋር ልትጫወት ትችላለህ፤ ነገር ግን በዚህ መልኩ ተሸንፎ ባለፉት ዓመታት የገነባነውን መልካም ስም ማበላሸት ግን ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም ብሏል።
ይህ የ7ለ 0 ውጤት የክሮኤሺያ ብሔራዊ ቡድን በእግር ኳስ ታሪኩ ያስመዘገበው የከፋ እና ትልቁ የሽንፈት ውጤት ኾኖ ተመዝግቧል።
ሞድሪች ቡድኑ አፋጣኝ መሻሻል በማሳየት በሚቀጥሉት ጨዋታዎች የቡድኑን ብቃት፣ ኩራት እና አንድነት ማስጠበቅ እንዳለበት አሳስቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here