የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) በጊኒ-ቢሳው የሚገኘውን “ኤስታዲዮ ናሲዮናል 24 ደ ሴቴምብሮ” ስታዲየም ከተጨማሪ የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ማገዱ ተገልጿል።
ውሳኔው የተላለፈው ጊኒ-ቢሳው በሀገሯ ከናይጄሪያ ጋር ባደረገችው እና 3 ለ 0 በተሸነፈችበት ጨዋታ የሜዳው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ እና ደካማ መኾን ከፍተኛ ቅሬታ በመቀስቀሱ ነው።
ካፍ ለናይጄሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይቅርታ የጠየቀ ሲኾን ስታዲየሙ ከጨዋታው በፊት በተደረገ ምርመራ ብቁ ኾኖ ተገኝቶ ፈቃድ ቢሰጠውም፣ ከጨዋታው በኋላ የሜዳው ሁኔታ መበላሸቱን ማብራሪያ ሰጥቷል።
ጊኒ-ቢሳው ከዚህ ቀደም በስታዲየሟ ደረጃ ማነስ ምክንያት የሜዳዋን ጨዋታዎች በሞሮኮ እንድታካሂድ ተገዳ የነበረ ቢኾንም ከተደረጉ የጥገና ሥራዎች በኋላ ስታዲየሙ እንደገና ጸድቆ ፈቃድ አግኝቶ ነበር። ኾኖም አሁን በተፈጠረው ችግር ምክንያት ዳግም እገዳ ተጥሎበታል።
በዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



