የቱርክ ብሔራዊ ቡድንን ምን ነካው?

0
10

 

በአውሮፖ ካሉ ሀገራ በእግር ኳስ ውበታቸውም ኾነ በውጤት ከጠንካራዎቹ የአውሮፖ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ነው የሚመደበው የቱርክ ብሔራዊ ቡድን። አሁን ግን ያ ማራኪ እግር ኳስ ያለው ጠንካራው የቱርክ ብሔራዊ ቡድን መኾን ተስኖት እየታየ ይገኛል።

ብሔራዊ ቡድኑ አሁን ላይ እየተካሄደ ባለው የኔሽንስ ሊግ ጨዋታ ላይ አስከፊ ጉዞን እያደረገ ይገኛል።

የቱርክ ብሔራዊ ቡድን በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ባደረጋቸው ያለፉት ሦሥት ጨዋታዎች በሙሉ መሸነፉ ቡድኑን ምን ነካው አስብሏል።

ቡድኑ እስካሁን ባደረጋቸው ጨዋታዎችም በፈረንሳይ 1ለ0፣ በጣሊያን4ለ1 እና በቤልጂየምደግሞ 3ለ0 ተሸንፏል።

ቡድኑ ባደረጋቸው ሦሥት ጨዋታዎችም 1 ግብ ብቻ አስቆጥሮ 8 ግቦችን ያስተናገደ እና ምንም ነጥብ ሳያስመዘግብ በምድቡ ሥር መገኘቱ የቡድኑ ችግር ሰፋ ያለ መኾኑን አሳይቷል።

ከአስከፊው የዓለም ዋንጫ ቆይታው በኋላ በኔሽንስ ሊጉም ተመሳሳይ ቀውስ ውስጥ የሚገኘው የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ወቅታዊ እንቅስቃሴ ደጋፊዎቹን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ጥሏል።

የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ አቅም ያላቸው ተጫዋቾች እና ጠንካራ ደጋፊዎች ያሉት ቢኾንም፣ በውጤት አለመረጋጋት የሚታወቅ ቡድን መኾኑ ነው ደጋፊዎቹን እያስከፋ ያለው።

ብሔራዊ ቡድኑ በ2002 የዓለም ዋንጫ በኮሪያ-ጃፓን በተካሄደው የዓለም ዋንጫ 3ኛ ደረጃን በመያዝ በታሪኩ ትልቁን የዓለም አቀፍ ውድድር ስኬት ያስመዘገበ ነው።

በዩሮ 2008 ላይም በመጨረሻ ደቂቃ ግቦች በሚታወቀው አስደናቂ አጫዋወቱ እስከ ግማሽ ፍጻሜ መድረስ ችሎ ነበር።

በቅርቡም ቢኾን በ2024ቱ የአውሮፓ ዋንጫ በወጣት ተጫዋቾች ታግዞ እስከ ሩብ ፍጻሜ በመጓዝ ጥሩ አቋም አሳይቷል።

ታዲያ ይህ ብሔራዊ ቡድን እንዴት የአቋም አለመረጋጋት ውስጥ ወደቀ ያሰኛል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_23_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here