በ2026 ዓለም ዋንጫ ድንቅ ብቃቱን በማሳየት የብዙዎችን ትኩረት የሳበው የኬፕ ቨርዴው ግብ ጠባቂ ቮዚኛ፣ ከውድድሩ በኋላ ዝነኛ መኾኑ ሕይወቱን እንዳከበደበት ለኦብዘርቨር’ተናግሯል።
ከዓለም ዋንጫው በኋላ ሰላሙን እና የግል ነጻነቱን እንዳጣ የገለጸው ቮዚኛ አሁን ላይ ወደ ውጭም ኾነ ወደ ምግብ ቤት በሚወጣበት ወቅት ሰዎች ለፎቶ እና ኦውቶግራፍ እንደሚጠይቁት፣ ይበልጥ ደግሞ ያለ ፈቃዱ በቪዲዮ እንደሚቀርጹት ገልጿል።
በውድድሩ ወቅት ከበርካታ ተቋማት የማስተዋወቅ ጥያቄ የቀረበለት ቢኾንም ከአንድ ድርጅት ጋር ብቻ መሥራቱን እና ወደፊትም የሰዎች ጤና ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ድርጅቶችን ማስተዋወቅ እንደማይፈልግ አረጋግጧል።
አክሎም ምርጫ ቢሰጠው ከዛሬው ዝነኛ ሕይወቱ ይልቅ የቀደመውን ሰላማዊ ሕይወቱን እንደሚመርጥ ገልጿል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_18_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



