የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ተጫዋቾች በልምምድ ማዕከል በሚቆዩበት ወቅት ጸጉራቸውን እንዳይቆረጡ ጥብቅ እገዳ ጣለ።

0
91

 

የፈረንሳዩ ሊኩይፕ’ ጋዜጣ እንዳስነበበው አዲሱ አሠልጣኝ ዚዳን ተጫዋቾች ትኩረታቸውን በሙሉ በሜዳ ላይ ጨዋታ እና ልምምድ ላይ ብቻ እንዲያደርጉ በመፈለጉ፣ ፀጉር አስተካካዮች ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ካምፕ እንዳይገቡ ከልክሏል።

በዚህም መሠረት የፈረንሳይ ተጫዋቾች ወደ ካምፕ ከመግባታቸው በፊት ጸጉራቸውን መስተካከል ማጠናቀቅ የሚጠበቅባቸው ሲኾን በካምፕ ቆይታቸው ወቅት ግን አዲስ የፀጉር ስታይል ማድረግ አይችሉም።

ዚዳን ከዚህ ቀደም ተጫዋቾች ወደ ካምፕ ሲገቡ የሚያደርጉትን የፋሽን አለባበስ የሚያሳይ የሚዲያ ሽፋን እና የካሜራ መገኘት መገደቡ የሚታወስ ሲኾን አዲሱ የፀጉር ቁርጥ እገዳም የቡድኑን ሥርዓት እና ዲሲፕሊን ለማጠናከር እንዲሁም ከሜዳ ውጭ ያሉ ትኩረት የሚስቡ ነገሮችን ለመቀነስ የተወሰደ እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_16_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here