የመጀመሪያው አፍሪካዊ አሠልጣኝ በቻምፒዮንስ ሊጉ።

0
107
በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ምሽቱን የተከናወነ ሲኾን ፒ ኤስ ጅ ስሎቫን ብራቲስ ላቫን 6ለ1 አሸንፏል::
ታዲያ በዚህ ጨዋታ የስሎቫኪያውን ቡድን በአሠልጣኝነት የመራው የቀድሞው የአይቮሪኮስት እና የማንችስተር ሲቲ ተጫዋች ያያ ቱሬ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ታሪክ የመጀመሪያው አፍሪካዊ አሠልጣኝ በመኾን አዲስ ታሪክ ሠርቷል።
ያያ ቱሬ ስሎቫን ብራቲስ ላቫን ባሳለፍነው ሰኔ ወር በዋና አሠልጣኝነት የተቀላቀለ ሲኾን በክለቡም ለቀጣይ ሦሥት ዓመታት ይቆያል።
ይህ የአፍሪካ ምርጡ ተጫዋች በአሠልጣኝነት ሥራው የዩክሬን፣ የሩሲያ እና የቤልጅየም ክለቦች ላይ በምክትል አሠልጣኝነት የሠራ ሲኾን በብሔራዊ ቡድን ደግሞ የሳዑዲ አረቢያ ብሔራዊ ቡድንን በምክትል አሠልጣኝነት መርቷል።
የአይቮሪኮስት እውቁ ተጫዋች ቱሬ ስሎቫን ብራቲስላቫን ከሁለት ጊዜ ተከታታይ የቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ፒኤስጂ ጋር ባደረጉት ጨዋታ በዋና አሠልጣኝነት በመምራት ለአፍሪካ ታሪካዊ ምሽት እንዲኾን አድርጓል።
በቴዎድሮስ ኃይለኢየሱስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here