የአራት ሰዓት ከ28 ደቂቃው ድንቅ ጨዋታ።

0
130
በዩኤስ ኦፕን የግራንድ ስላም የሜዳ ቴኒስ ጨዋታ ንጋት ላይ የተደረገው መርሐግብር በውድድሩ ታሪክ ረጅም ሰዓታትን ከቆዩት መካከል ኾኗል፡፡
ወደ ግማሽ ፍጻሜው ለመግባት በነበረው ወሳኝ ጨዋታ አሜሪካዊው ቤን ሸልተን ከስፔኑ ኃያል ሃርሎስ አልካራዝ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ድል በማድረግ የመጨረሻ አራቱ ውስጥ ገብቷል፡፡
ከጉዳት በኋላ የሜዳ ቴኒስ ውድድሩን አሜሪካ ላይ ያደረገው አልካራዝ በመጨረሻም እጅ ሰጥቷል፡፡ ከአራት ሰዓት ከ28 ደቂቃዎች በላይ በተካሄደው በዚህ አጓጊ ጨዋታ ከፍተኛ ተመልካች ፉክክሩን ተመልከቷል፡፡
ጨዋታውንም የዓለም ቁጥር 8 ኾኖ የጀመረው ቤን ሸልተን 6-7 (5-7)፣ 6-1፣ 6-3፣ 1-6፣ 7-6 (10-7) በኾነ 5 ለ 2 በኾነ ውጤት ማሸነፉን አረጋግጧል፡፡ ይህ ስኬት ለ23 ዓመቱ ወጣት ትልቁ ድል ኾኖም ተመዝግቦለታል።
ሼልተን ከዚህ ቀደም ከምርጥ ሦሥት ውስጥ ካሉ ተጫዋቾች ጋር 17 ጊዜ ተጫውቶ ማሸነፍ አልቻለም ነበር። እንዲሁም ከስፔናዊው አልካራዝ ጋር ያደረጋቸውን ሦሥቱንም ያለፉ ጨዋታዎች ተሸንፏል።
ሸልተን ጨዋታውን በድል ካጠናቀቀ በኋላ በሜዳ ላይ ያሳየው የአዕምሮ ጥንካሬ እና ትኩረት ለዚህ ውጤት እንዳበቁት ተናግሯል። “ከእንደዚህ አይነት ታላቅ ተጫዋች ጋር መጫወት ሁልጊዜም ፈታኝ ነው። ዛሬ ግን የኔ ቀን እንዲኾን ጠንክሬ ሠርቻለሁ፣ ይህ ድል ለቀጣይ ጉዞዬ ትልቅ ብርታት ይሰጠኛል” ሲል ገልጿል።
ይህ ድል አሜሪካ ከ23 ዓመታት በኋላ በዩኤስ ኦፕን የወንዶች ነጠላ ፉክክር ሻምፒዮናነትን ለማግኘት ያላትን ተስፋ ይበልጥ አጠናክሮላታል።
ያለፈው ዓመት የመድረኩ ባለድል አልካራዝ ከረጅም የእጅ ጉዳት እና ከእረፍት መልስ በተሳተፈበት የመጀመሪያ ውድድሩ ላይ ድል አልቀናውም፡፡
ሌላኛው አሜሪካዊ ፍራንሲስ ቲፋው ወደ ግማሽ ፍጻሜ የገባ ተጫዋች ነው፡፡ በዚህ ዙርም ከቤን ሸልተን ጋር የሚጫወት ይኾናል፡፡
በሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here