ጆሴ ሞሪንሆ ከ2010 እስከ 2013 በሪያል ማድሪድ በቆዩባቸው ሦሥት የውድድር ዓመታት ቡድኑን ወደ ጠንካራ ደረጃ የመለሱ ቢኾንም የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ግን ማሳካት አልቻሉም።
በሦሥቱም የውድድር ዓመታት ቡድኑን እስከ ግማሽ ፍጻሜ ማድረስ የቻሉ ቢኾንም በትናንሽ ስህተቶች ምክንያት በባርሴሎና፣ ባየርን ሙኒክ እና ቦሪሽያ ዶርትሞንድ ተሸንፈው ተሰናብተዋል።
ራሳቸውን ዘ ስፔሻል ዋን ብለው በሚጠሩበት በዚያ ወርቃማ ዘመን ለሻምፒዮንስ ሊግ ቅርብ ከኾነው ሪያል ማድሪድ ጋር ዋንጫውን አለማሳካታቸው ከታክቲክ እና መልበሻ ክፍል ጋር በተያያዘ ክፍተቶች እንደነበሩባቸው ይገለጻል።
በወሳኝ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ ሞሪንሆ ከመጠን በላይ ለተከላካይ ክፍሉ ቅድሚያ የሚሰጡበት ታክቲክ የሪያል ማድሪድን የማጥቃት አቅም ገድቦታል በሚል ይወቀሱ ነበር።
በዚያ ወቅት ባርሴሎና በታሪክ ከታዩ የዓለማችን ምርጥ ቡድኖች አንዱ የነበረ ሲኾን ሞሪንሆም ከባርሴሎና ጋር በሚደርጉት ጥብቅ ፉክክር እና የሥነ ልቦና ጦርነት ላይ ትኩረታቸውን እንዳባከኑ ይነገራል።
በመጨረሻ ዓመታቸው ከቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች እንደ ኢከር ካሲያስ፣ ሰርጂዮ ራሞስ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር የነበራቸው አለመግባባት የቡድኑን አንድነት እና ትኩረት ጎድቶት ነበር።
ጆሴ ሞሪንሆ ዘንድሮ ከ13 ዓመታት በኋላ በሳንቲያጎ በርናባው ያልጨረሱትን የቤት ሥራ የሚቋጩበት ወርቃማ ዕድል እጃቸው ገብቷል።
ዛሬ በሚጀምረው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ በሜዳቸው እና በደጋፊያቸው ፊት የጣሊያኑን ክለብ ኢንተር ሚላንን በማስተናገድ ርምጃቸውን ይጀምራሉ።
በታደሠ ሙላት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



