ዘንድሮ ከምንጊዜውም በተሻለ ባሎንዶርን የሚያሸንፍበት አቋም ላይ እንደሚገኝ ኬልያን ምባፔ ተናገረ።

0
111

 

የ27 ዓመቱ የሪያል ማድሪድ አጥቂ ባለፈው የውድድር ዓመት ለክለቡ በተሰለፈባቸው 44 ጨዋታዎች 42 ግቦችን አስቆጥሯል።

ሪያል ማድሪድ ግን ዓመቱን ያለምንም ዋንጫ ነው ያጠናቀቀው።

ከክለብ ባሻገር በብሔራዊ ቡድን ደረጃም ድንቅ የብቃት ጊዜን ያሳለፈው ኬልያን ምባፔ በዓለም ዋንጫ ምንም እንኳን ሀገሩ ፈረንሳይ 4ኛ ደረጃን ይዛ ብታጠናቅቅም እርሱ በግሉ በ10 ግቦች የወርቅ ጫማ አሸናፊ ኾኗል።

የምንጊዜም የዓለም ዋንጫ ከፍተኛ ግብ አግቢነት ክብረወሰንንም በ22 ግቦች ተረክቧል።

እናም በዓመቱ ውድድር ባሳየው በዚህ ድንቅ ብቃት የባሎንዶር አሸናፊነት ይገባኛል ሲል በልበ ሙሉነት ተናግሯል።

ምባፔ ከዚህ በፊት በባሎንዶር ሽልማት ያገኘው ከፍተኛ ደረጃ 2023 ላይ 3ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀበት ነው።

ዘንድሮ ግን በጥቅምት ወር መጨረሻ በሚካሄደው የዓለም ኮከብ ተጫዋች ሽልማት ለአሸናፊነት ግምት ካገኙ ተጫዋቾች አንዱ መኾኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጳጉሜን_02_2018_ዓ_ም

በኃይሌ አበራ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here