ሴስክ ፋብሬጋስ የ2025/26 የውድድር ዘመን የሴሪ አ የዓመቱ ምርጥ አሠልጣኝ ተባለ።

0
103
አሠልጣኝ ፋብሬጋስ ይህንን ታላቅ ክብር ያገኘው ምሽቱን በተካሄደው የጣሊያን እግር ኳስ ማኅበር የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ነው።
ፋብሪጋዝ በቅርብ ጊዚያት ወደ ዋናው ሊግ ያደገውን የኮሞ እግር ኳስ ክለብን አስደናቂ በኾነ ሁኔታ በጣሊያን ሴሪ አ 4ኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ አድርጓል።
በዚህም ክለቡ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እንዲሳተፍ በማስቻል ታሪክ ሠርቷል።
የቀድሞው የአርሰናል እና ባርሲሎና አማካይ በ2023 በዚሁ ክለብ እግር ኳስን መጫወት ካቆመ በኋላ በሦሥት ዓመት ውስጥ ከረዳት እና ጊዜያዊ አሠልጣኝነት ተነሥቶ የሊጉ ምርጥ አሠልጣኝ ለመኾን በቅቷል።
የሴሪ ኤ ሻምፒዮኖቹ ኢንተር ሚላን የግራ መስመር ተመላላሽ ፌድሪኮ ዲማርኮ ደግሞ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተሸልሟል።
ዲማርኮ በውድድር ዓመቱ በሊጉ ሰባት ግቦች እና 16 የግብ ኳሶችን ማመቻቸት ችሏል።
በሰኢድ ኢብራሂም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here