የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ለአሊሰን ቤከር ተተኪ ይኾናል የተባለውን ቤልጀማዊ ግብ ጠባቂ ወደ አንፊልድ ለማምጣት ተስማምቷል።
1ሜትር ከ99ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው የ18 ዓመቱ ወጣት ግብ ጠባቂ ሉካ ብሩግማንስ 35 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ሂሳብ ወጥቶበታል።
በጆርጂያዊው ማማርዳሽቬሊ ዕምነት ያጡት ቀዮቹ በቤልጀማዊው ወጣት ተማምነዋል።
አሁን ላይ ብሩግማንስ ለቤልጅየሙ ጌንክ ክለብ የሚጫወት ሲኾን 2027 ላይ የመመርሲሳይዱን ክለብ ሊቨርፑል ይቀላቀላል ነው የተባለው።
በታደሠ ሙላት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



