ፒየር-ኤምሪክ ኦባምያንግ ለአዲሱ ክለብ ግብ አስቆጥሯል፡፡

0
12
ዴፖርቲቮ ላኮሩኛ ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ላሊጋ ተመልሶ የመጀመሪያ ጨዋታውን ትናንት ምሽት ሲያደርግ ከኤልቼ ጋር 1 ለ 1 ተለያይቷል።
የ2000 የላሊጋ ሻምፒዮን የነበረው ዴፖርቲቮ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ለአራት የውድድር ዘመናት በሀገሪቱ ሦስተኛ ሊግ ውስጥ ለማሳለፍ ተገድዶ ነበር።
በደጋፊው ፊት የተጫወተው ላካሩኛ በአዲሱ ፈራሚ የ37 ዓመቱ የቀድሞ የአርሰናል እና ባርሴሎና አጥቂ ፒየር-ኤምሪክ ኦባምያንግ አስደናቂ ጎል ቀዳሚ ሆኗል፡፡
ኦባምያንግ በሐምሌ ወር ማርሴይን ለቆ ዴፖርቲቮን የተቀላቀለ ሲሆን፣ ክለቡ በላሊጋ የመቆየት ተስፋውን እንዲያሳካ ትልቅ እገዛ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
በጨዋታው ዴፖርቲቮ መሪነቱን ጠብቆ መውጣት አልቻለም። 76ኛ ደቂቃ ላይ ማርክ አጉዋዶ ኤልቼን አቻ አድርጓል።
ሰኢድ ኢብራሂም
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here