ቼልሲ አማካዩን ኤንዞ ፈርናንዴዝን ወደ ሲቲ ለማዘዋወር የጊዜ ገደብ አስቀመጠ።

0
33

ማንችስተር ሲቲ አማካዩን ኤንዞ ፈርናንዴዝን ለማዘዋወር ጥረት እያደረገ ይገኛል።

የተጫዋቹ ባለቤት ቼልሲ ተጫዋቹን ለማዘዋወር ስምምነቱን እንዲያጠናቅቅ እስከ አርብ የጊዜ ገደብ አስቀምጧል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ለተጫዋቹ ያስቀመጠው የ120 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋ በዚህ ሳምንት መጨረሻ በሚጠናቀቀው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካልተከፈለ አርጀንቲናዊው አማካይ ከክለቡ እንደማይለቅ ገልጿል።

እንደ ያሆ ስፖርት ዘገባ ቼልሲ ይህን የጊዜ ገደብ ለሲቲ እና ለፈርናንዴዝ ወኪሎች ማስተላለፉን እንዲሁም ከግንቦት ወር ጀምሮ ለፈርናንዴዝ ወኪል የተጫዋቹ ዋጋ እንደተነገረው ነው የገለጸው።

#AMECO #sport

#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_07_2018_ዓ_ም

በጥበቡ ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here