በእግር ኳስ ዓለም ውስጥ አዳዲስ ኮከቦች በየዘመኑ እንደ ማለዳ ፀሐይ ብቅ ይላሉ። አንዳንዶቹ እንደ አብሪ ኮከብ በቅጽበት ደምቀው ይጠፋሉ። ጥቂቶቹ ደግሞ ለረጂም ጊዜ የሚያበሩ ድንቅ ፈርጦች ኾነው ይቆያሉ።
በወጣትነት ዕድሜው የመጫወቻ ሜዳውን በግርማ ሞገሱ የተቆጣጠረው እና የበርካታ ስፖርት አፍቃሪያንን ቀልብ የገዛው እንግሊዛዊው የካሪዝማቲክ አማካይ ጁድ ቤሊንግሃም ከእነዚህ ብርቅዬ ፈርጦች መካከል አንዱ ነው። ገና በ20ዎቹ መጀመሪያ ዕድሜ ላይ ይገኛል። ጁድ ቤሊንግሃም በዘመናዊው እግር ኳስ ውስጥ የራሱን ደማቅ ታሪክ በወርቃማ ብዕር እየጻፈ ይገኛል።
ከበርሚንግሃም ሲቲ የታዳጊ ቡድን ተስፋነት ተነስቶ በቦሩሲያ ዶርትሙንድ በኩል አልፎ ዛሬ በዓለም ግዙፉ ክለብ ሪያል ማድሪድ እና በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ዋናው ሞተር ለመኾን በቅቷል።
🔗 እንደ ቢቢሲ እና ስካይ ስፖርት መረጃ በ2019 በ16 ዓመቱ ለበርሚንግሃም ሲቲ በመሰለፍ የክለቡ ታሪክ ትንሹ ተሰላፊ እና ግብ አግቢ ለመሆን በቃ። ክለቡን ሲለቅም የነበረውን የ22 ቁጥር ማሊያ በማሳረፍ ታሪክ ሠርቷል።

በቦሩሲያ ዶርትሙንድ በነበረው ድንቅ ቆይታ የ2022/23 የቡንደስሊጋው የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ክብርን ተጎናጽፏል። ወደ ሪያል ማድሪድ ከተዘዋወረ በኋላ በመጀመሪያው የውድድር ዘመን 2023/24 የላሊጋ እና የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን በማንሳት በ36 ጨዋታዎች 23 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። የዓለምን ምርጥ ወጣት ተጫዋች የሚያስብሉትን የ2023 ኮፓትሮፒ (Kopa Trophy) እና የጎልደንቦይ (Golden Boy) አዋርዶችን በበላይነት አሸንፏል።
🎨 የጨዋታ ስታይል እና የመሪነት ብቃቱ ልዩ ነው። የሪያል ማድሪድ አሠልጣኝ የነበሩት ካርሎ አንቸሎቲ በአንድ ወቅት ቤሊንግሃም ሜዳ ውስጥ ሲገባ ተጫዋች ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የቡድኑ አዛዥ እና መሪ ጭምር እንጂ ብሎ ነበር።
🧠 ከፍተኛ የጨዋታ ብስለት አለው። ዕድሜው ወጣት ቢኾንም ሜዳ ውስጥ የሚያሳየው ውሳኔ ሰጪነት እና የመሪነት ባህሪ የአንጋፋ ተጫዋቾችን ያህል የጎለበተ ነው።
✨ ጁድ ቤሊንግሃም በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከታላላቆቹ ኮከቦች ተርታ የመሰለፍ ዕድል ይኖረው ይኾን?
💬 አስተያየትዎን በኮመንት ላይ ያስቀምጡልን👇
#አሚኮ #FootballNews #ስፖርት
#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_06_2018_ዓ_ም
✍️ በሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



