“ለማንቸስተር ዩናይትድ ያለኝን ፍቅር ለመግለጽ ከዚህ ውጭ መንገድ አላገኘሁም”

0
84
ማርክስ ራሽፎርድ ለማንቸስተር ዩናይትድ ያለውን ፍቅር በጀርሲ ቁጥሮቹ ንቅሳት ገልጿል።
የማንቸስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጫዋች ማርከስ ራሽፎርድ ለክለቡ ያለውን ጥልቅ ፍቅር እና ቁርጠኝነት በሚገልጽ መልኩ እስካሁን ለቀይ ዲያብሎሶቹ የለበሳቸውን የጀርሲ ቁጥሮች በሰውነቱ ላይ ተነቅሷል።
ተጫዋቹ ቀደም ሲል ሲጠቀምባቸው የነበሩትን ቁጥር 39፣ 19 እና 10 በንቅሳት መልክ ያስቀረ ሲኾን በቀጣይም አዲሱን የጀርሲ ቁጥር 14 እንደሚረከብ ተገልጿል።
ማንቸስተር ዩናይትድ በተጫዋቹ ላይ ሙሉ ዕምነት የጣለ ሲኾን ራሽፎርድ በኦልድትራፎርድ የመቆየት ዕድሉ ከፍተኛ መኾኑ ተመላክቷል።
ይህ እርምጃም ራሽፎርድ ለክለቡ ያለውን ልዩ ቁርጠኝነት እና ማንቸስተር ዩናይትድ ለእሱ ምን ያህል ትልቅ ትርጉም እንዳለው ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
ማርክስ ራሽፎርድ ለስካይ ስፖርት እንዳለው ለማንቸስተር ዩናይትድ ያለኝን ፍቅር ለመግለጽ ከዚህ ውጭ መንገድ አላገኘሁም ብሏል።
✍️በምሥጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here