ኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የዓለም ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስመዘገበች። በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ባለው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና፤ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር ኢትዮጵያ የወርቅና ብርና ሜዳሊያ አግኝታለች።
አትሌት አልማዝ ዮሃንስ ርቀቱን በ9:15.81 በሆነ ጊዜ ቀዳሚ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች።
አትሌት ወሰኔ አሰፋ ደግሞ 9:30.50 በሆነ ጊዜ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች።
ኢትዮጵያ እስካሁን በውድድሩ አንድ የወርቅ ፣ ሁለት የብር እና አንድ የነሀስ ሜዳልያ አግኝታለች።
#አሚኮ #Ethiopia #WirldAthletics



