ኢትዮጵያውያን ለሜዳሊያ የሚጠበቁበት ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሰዓታት ቀርተውታል።

0
66
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም አቀፉ የወጣቶች አትሌቲክስ መሳተፍ የጀመረችው እ.ኤ.አ. በ1986 በአቴንስ፣ ግሪክ በተካሄደው የመጀመሪያው የሻምፒዮና ውድድር ላይ ነው።
ታደሰ ገብሬ እና ነጋሽ ዱቤ ወርቅ እና ብር በ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ፤ ደበበ ደምሴ በ10 ሺህ ሜትር ነሐስ በማምጣት ባጠቃላይ በ1 ወርቅ በ1 ብር እና በ1 ነሐስ ከዓለም 14ኛ ከአፍሪካ ደግሞ ኬንያ እና ናይጀሪያን በመከተል 3ኛ ኾና በማጠናቀቅ በወጣቶች ሻምፒዮናን ጀምራለች።
በ40 ዓመት ምሥረታው 21ኛ መድረኩን ከሰዓታት በኋላ የሚጀምረው የዓለም ከ20 ዓመት በታች ወጣቶች ሻምፒዮና በአሜሪካዋ ኦሪገን ግዛት ዩጅን ከተማ በዝነኛው ሀይዋርድ ፊልድ ስታዲየም ይከናወናል።
ከ16 እስከ 19 ዓመት ድረስ የኾኑ አትሌቶች ከሐምሌ 29/2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም በሚቆየው ውድድር ከ147 ሀገራት የተወጣጡ 1ሺህ 800 አትሌቶች ይሳተፉበታል።
የዓለም አትሌቲክስ ባወጣው የውድድሩ የጊዜ ሰሌዳ መሠረትም ኢትዮጵያውያንን የወከሉ 16 አትሌቶች ይሳተፋሉ።
በዛሬው የውድድሩ የመጀመሪያ ቀን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ4 ዘርፎች በሁለቱ ጾታ በ800ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ እንዲሁም የሴቶች 3ሺህ መሰናክል እና የሴቶች 5ሺህ ሜትር ፍጻሜ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለሜዳሊያ የሚጠበቁባቸው ናቸው።
በሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here