ሪያል ማድሪድ ሮድሪን ለማስፈረም ከማንችስተር ሲቲ ጋር ግንኙነት ጀመረ።

0
80
ሪያል ማድሪድ ሮድሪን ለማስፈረም ከማንችስተር ሲቲ ጋር ግንኙነት ጀምሯል።
የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፊዮርቲኒዮ ፔሬዝ ከተጫዋቹ ወኪሎች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በክለቦቹ መካከል ለሚደረገው ይፋዊ ግንኙነት ፈቃድ ሰጥተዋል።
ሮድሪ ወደ ሪያል ማድሪድ የመዛወር ሕልም አለው። ተጫዋቹ ለማድሪድ ለመፈረም ግፊት ሲያደርግ ቆይቷል። ሪያል ማድሪዶች ለሮድሪ ዝውውር ከ50 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ለመክፈል ዝግጁ መኾናቸውን ለማንቸስተር ሲቲ አስታውቀዋል።
ማንቸስተር ሲቲ እስከአሁን ምላሽ አለመስጠቱም ተዘግቧል።
በሌላ ዜና ዳኒ ዌልቤክ እስከ 2028 በሚቆይ ኮንትራት ለቼልሲ ለመፈረም መስማማቱ ተገልጿል።
በክለቦቹ መካከል እና በተጫዋቹ በኩል ስምምነቱ መጠናቀቁ ተመላክቷል። የሕክምና ምርመራውን በቅርቡ ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል።
#አሚኮ#ስፖርት
#ባሕር_ዳር#ሐምሌ_22_2018 ዓ_ም
በያየህ ፈንቴ

See

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here