ዝቋላ ከነማ የኽምራ ሊግ ሻምፒዮን ኾነ።

0
103

 

በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ለተከታታይ 10 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የኽምራ ሊግ የክለቦች ሻምፒዮና በዝቋላ ከነማ አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

ስምንት ክለቦች በሁለት ምድብ ተከፍለው ያካሄዱት ይህ ውድድር በፍጻሜው ዝቋላ ከነማን ከተከዜ አናብስት ጋር አገናኝቷል።

የመደበኛው የጨዋታ ጊዜ 1 ለ 1 በኾነ ውጤት ተጠናቅቋል።

በተሰጠው የመለያ ምትም ዝቋላ ከነማ 6 ለ 5 በመርታት የመጀመሪያውን ዋንጫ አሳክቷል።

የውድድሩ የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ ለ204ኛ ኮር ክለብ ተሰጥቷል።

ተጫዋቾች ለሊጉ የተደረገው በቂ ዝግጅት ለውጤት እንዳበቃቸው ገልጸዋል። ውድድሩ በስፖርቱ ማደግ ለሚፈልጉ ባለክህሎት ታዳጊዎች ትልቅ ዕድል የሚከፍት መኾኑን ጠቁመዋል።

የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ይርጋ ማርዬ ውድድሩ አንድነት እና ስፖርታዊ ጨዋነት ጎልቶ የታየበት መኾኑን ገልጸዋል። አሸናፊው ክለብ በቀጣይ በክልሉ ሻምፒዮና ላይ ዋግኽምራን ወክሎ ለሚያደርገው ውድድር ከወዲሁ እንዲዘጋጅ አሳስበዋል።

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት #የኽምራሊግ

#ሰቆጣ_ሐምሌ11_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here