“ለሴት አሠልጣኞች አዲስ ዕድል ሲሰጥ የችሎታ እንጂ የኮታ ጉዳይ አይደለም”

0
100
⚽️
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) እና ከዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የሚተላለፉ ውሳኔዎችን በመቀበል በተግባር እያዋለ ይገኛል።
በዚህም መሰረት በሚቀጥለው የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ ሴቶች ሊግ ላይ ለሚሳተፉ ክለቦች አዲስ እና አስገዳጅ መመሪያ አጽድቋል።
መመሪያው ክህሎት እያላቸው ዕድል ላጡ ሴት አሠልጣኞች ሰፊ የሥራ በር የሚከፍት ነው።
📋 በአዲሱ መመሪያ መሠረት ከሚቀጥለው የውድድር ዓመት ጀምሮ በኢትዮጵያ ሴቶች የሊግ እርከን ላይ የሚገኙ ክለቦች በግዴታ ሴት አሠልጣኞችን መቅጠር ይኖርባቸዋል።
🏟️ የተቀጣሪዎቹ ሴት ባለሙያዎች ሚና በዋና አሠልጣኝነት አሊያም በምክትል አሠልጣኝነት ደረጃ የሚወሰን ይኾናል።
🔓 ይህ ውሳኔ የሙያ ፈቃድ ኖሯቸው በቤት ውስጥ የተቀመጡ እና ዕድል የተነፈጉ በርካታ ሴት አሠልጣኞችን ወደ ሜዳ የሚያወጣ ነው።
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሴቶች ልማት ዴስክ ኀላፊ በኃይሏ ዘለቀ እንዳሉት ይህ ውሳኔ በየጊዜው የሙያ ፈቃድ ሥልጠና እየወሰዱ ወደ ጎን የተገለሉ እና ዕውቀት ያላቸው አዳዲስ አሠልጣኞችን የምናገኝበት ይኾናል ብለዋል።
🎖️ዕድሉ ቢሰጥም ቅጥሩ የሚፈጸመው በችሎታ ላይ ተመስርቶ ብቻ እንደኾነ ተገልጿል። ሴት አሠልጣኞች በክለቦቻቸው የሚመረጡት ለፆታ ማሟያ (ኮታ) ብቻ ሳይኾን፣ ያላቸውን እውቀት እና ብቃት አስመስክረው ብቻ እንደሚኾንም ኀላፊዋ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ይህንን የወጣውን አዲስ መመሪያ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቋል።
#ባሕር_ዳር፡ ሐምሌ 9/2018 ዓ.ም
ዘጋቢ: ✍️ ዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here